2 Chronicles 15

ንጉሥ አሳ ያደረገው ተሐድሶ

15፥16-19 ተጓ ምብ – 1ነገ 15፥13-16 1የእግዚአብሔር መንፈስ በዖዴድ ልጅ በአዛርያስ ላይ መጣ። 2እርሱም አሳን ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፤ “አሳ፣ እናንተም ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፤ አድምጡኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ፣ እርሱም ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉት ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን፣ ይተዋችኋል። 3እስራኤል ያለ እውነተኛ አምላክ፣ ያለ አስተማሪ ካህንና ያለ ሕግ ብዙ ዘመን አሳልፈዋል። 4በመከራቸው ጊዜ ግን፣ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው። 5በዚያን ዘመን በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ ታላቅ ሁከት ስለ ነበር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት አስተማማኝ አልነበረም። 6እግዚአብሔር በተለያየ መከራ ያስጨንቃቸው ስለ ነበር፣ አንዱ መንግሥት በሌላው መንግሥት፣ አንዱም ከተማ በሌላው ከተማ ይደመሰስ ነበር። 7እናንተ ግን የድካማችሁን ዋጋ ስለምታገኙ በርቱ፤ እጃችሁም አይላላ።”

8አሳ ይህን ቃልና የነቢዩን የዖዴድን ልጅ
የቩልጌትና የሱርስቱ ቅጅ (እንዲሁም ቍጥር 1) ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ዕብራይስጡ ግን የዖዴድን ልጅ የሚለውን አይጨምርም።
የዓዛርያስን ትንቢት በሰማ ጊዜ በረታ። ከመላው ይሁዳና ከብንያም ምድር፣ በኤፍሬምም ኰረብታዎች ላይ ከያዛቸው ከተሞች አስጸያፊዎቹን ጣዖታት አስወገደ። ከእግዚአብሔር መቅደስ ሰበሰብ ፊት ለፊት የነበረውንም የእግዚአብሔር መሠዊያ ዐደሰ።

9አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መሆኑን ባዩ ጊዜ፣ ከእስራኤል ብዙ ሰዎች እርሱን ተጠግተው ነበር፤ እርሱም ይሁዳንና ብንያምን እንዲሁም ከኤፍሬም፣ ከምናሴና ከስምዖን መጥተው ከእነርሱ ጋር የተቀመጡትን ሰበሰበ።

10እነርሱም በአሳ ዘመነ መንግሥት በዐሥራ አምስተኛው ዓመት፣ በሦስተኛው ወር በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። 11በዚያን ጊዜ በምርኮ ካመጡት ውስጥ ሰባት መቶ በሬ፣ ሰባት ሺሕ በግና ፍየል ለእግዚአብሔር ሠዉ። 12የአባቶቻቸውንም አምላክ እግዚአብሔርን በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ይሹ ዘንድ ቃል ኪዳን አደረጉ። 13የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ ሁሉ ግን፣ ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ ወንድም ሆነ ሴት እንዲገደል አደረጉ። 14ይህንም በታላቅ ድምፅ፣ በእልልታ፣ በእንቢልታና በመለከት ድምፅ ለእግዚአብሔር ማሉ። 15በፍጹም ልባቸው ስለማሉም የይሁዳ ሕዝብ በመሐላው ደስ ተሰኙ። እግዚአብሔርን ከልብ ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በሁሉም አቅጣጫ ዕረፍት ሰጣቸው።

16እንዲሁም ንጉሥ አሳ አያቱን ማዓካን ለአስጸያፊዋ የአሼራ ጣዖት ዐምድ ስላቆመች ከእቴጌነት ክብሯ ሻራት። አሳም ዐምዱን ቈርጦ በመሰባበር በቄድሮን ሸለቆ አቃጠለው። 17ምንም እንኳ ማምለኪያ ኰረብታዎችን ሙሉ በሙሉ ከእስራኤል ባያስወግድም፣ የአሳ ልብ በዘመኑ ሁሉ ፈጽሞ ለእግዚአብሔር የተገዛ ነበር። 18እርሱና አባቱ የቀደሱትን ብሩን፣ ወርቁንና ልዩ ልዩ ዕቃ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገባ።

19እስከ ሠላሳ አምስተኛው የአሳ ዘመነ መንግሥት ድረስ ምንም ዐይነት ጦርነት አልነበረም።

Copyright information for AmhNASV